እንኳን ወደ እንጅባራ ከተማ በደህና መጡ

መገኛ

የእንጅባራ ከተማ የምትገኘው በሰሜን  ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አዊ ዞን ከአዲስ አበባ በ 420 ኪ.ሜ ከክልሉ መንግሥት መቀመጫ ከሆነችው ባህርዳር ከተማ ደግሞ 176 ኪ.ሜ፣ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ 10º 53’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 36º 56’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡

አመሰራረት

እንጅባራ ከተማ የተቆረቆረችው በ 1884 ዓም ነው፡፡

የከተማ ማኔጅመንትና ፕላን 

እንጅባራ  በክልሉ  ከሚገኙ የሪፎርም  ከተሞች አንዷ ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣  ማዘጋጃ ቤት፣ 2 የከተማና 1 የገጠር ቀበሌዎች አላት፡፡ በ2003 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡