እንኳን ወደ ጎንደር ከተማ በደህና መጡ

1.1 መገኛ

ጎንደር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ከአዲስ አበባ  በ 747 ከክልሉ ዋና ከተማ በሕርዳር በ 170 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 12º 45’  ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º45’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ላይ ነው፡፡

1.2 አመሠራረት

ጎንደር ከተማ የተቆረቆረችው በ1636 ዓ. ም ጎንደር በክልሉ የሪፎርም  ከተሞች አንድዋ ስትሆን  የከተማ አስተዳደር፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 12 ክ/ከተማዎች፣ 12 የከተማ ቀበሌዎችና  10 የገጠር ቀበሌዎችን  አሷት፡፡ በ1997 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላን አላት፡፡