እንኳን ወደ ባህርዳር ከተማ በደህና መጡ

1.1 መገኛ

ባሕርዳር  ከተማ  የምትገኘዉ  በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ  ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’  በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ  ነው፡፡

1.2 አመሠራረት

ባሕርዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡  ባሕርዳር  በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም  ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤  የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣  የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች  አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡