- adminbeza
- [post-views]
ምናሌ
እንኳን ወደ ደሴ ከተማ በደህና መጡ
1.1 መገኛ
ደሴ ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ኢትዮጲያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በደቡብ ወሎ ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ400 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 08’ ሰሜን ላቲቲውድ እና በ39º38’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡
1.2 አመሠራረት
ከተማዋ የተቆረቆረች በ1875 ዓ. ም ነው፡፡ ደሴ በክልሉ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን የከተማ አስተዳደር፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 10 የከተማ ቀበሌዎችና 6 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ በ 2002 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላን አላት፡፡