- adminbeza
- [post-views]
ምናሌ
እንኳን ወደ ደብረማርቆስ ከተማ በደህና መጡ
1.1 መገኛ
የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ዞን ከአዲስ አበባ በ 300 ኪ.ሜ ከባህር ዳር ደግሞ 265 ኪ.ሜ፣ በ 37021’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 43’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡
1.2 አመሰራረት
ደብረማረቆስ ከተማ የጎጃም ገዥ በነበሩት ደጃዝማቸ ተድላ ጓሉ በ1845 ዓም የተቆረቆረች ሲሆን የከተማዋም መጠሪያ መንቆረር ይባል ነበር፡፡ በ 1872 ዓም ወደ ሥልጣን የመጡት ንጉስ ተክለሃይማኖት ካሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ የከተማዋ ስያሜ መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማረቆስ እንዲሆን አዋጅ በማስነገራቸው የከተማዋ መጠሪያ ሊሆን በቃ፡፡ ደብረማርቆሰ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ናስትሆን ከተማዋ በስሯ 6 ቀበሌዎችና ማዘጋጃ ቤት ያሉት የከተማ አስተዳደር አላት፡፡ በ2002 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡