- adminbeza
- [post-views]
ምናሌ
እንኳን ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ በደህና መጡ
1.1 መገኛ
ደብረብርሃን ከተማ የምትገኘው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ በ130 ኪ.ሜ፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ በ695 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ 11º 06’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 39º 45’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡
1.2 አመሰራረት
የደብረብርሃን ከተማ የተቆረቆረችው በ 1446 ዓም ነው፡፡ደብረብርሃን በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ማዘጋጃ ቤትና 5 ንዑስ ቀበሌዎች አላት፡፡ በ1984 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡